በከሳሽ ሙሉቀን ጌትነት እና በተከሳሽ ወ/ሮ አበባ በላቸው መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በአጼ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በማራኪ ቀበሌ በሟች ጌትነት ደሴ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ፤ ካርታ ቁጥር 25699 በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ እስጢፋኖስ፣ በምስራቅ ወንዳለ እና በምእራብ ያምሮት ተዋስኖ የሚገኘው እና 150 ካ.ሜ ላይ የተሰራ G+1 የሆነ ቤት በመነሻ ዋጋ 5‚444‚940.41 / አምስት ሚሊዩን አራት መቶ አርባ አራት ሽህ ዘጠኝ መቶ አርባ ብር ከአርባ አንድ ሳንቲም / ሆኖ ነሀሴ 23/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡00 በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በሰአቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የመጨረሻው አሸናፊ ያሸነፈበትን ¼ኛውን ወዲያውኑ በሞ/85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ዳርና አካ/ከፍ/ፍ/ቤት