- የገርባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ መሬት ባንክና ፋይናንሲንግ ልማት ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል 200 ካሬ ሜትር ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ12/09/2016 ዓ/ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በገርባ ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መግዛት የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ12/09/2016 ዓ/ም እስከ 23/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ23/09/2016 ዓ/ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሀ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ26/09/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 በገርባ ከተማ መሪ ማ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጋዜጣ እንዲሁም በገርባ ከተማ መሪ ማ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በሣይት ፕላን በተገለፀው እና በከተማው መዋቅራዊ ፕላን መሰረት ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ መገንባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ 0920780008፣ 0906416921፣ 0912967158 ወይም 0334540304 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡