በደቡብ ጎንደር ታች ጋይንት ወረዳ በአርብ ገበያ ከተማ መሪ/ማ/ቤት በ2017 በጀት አመት በከተማው ውስጥ የሚገኙትን የመኖሪያ፣ የድርጅት እና የመጋዘን ቦታዎችን በአዋጅ ቁጥር 721/2004 በደንብ ቁጥር 103/2004/ አንቀጽ 13/2 በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀጽ 17 በሚያዘው መሰረት በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በአርብ ገበያ ከተ/መሪ/ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡ የጨረታ ፖስታውን ቢሮ ቁ. 1 በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 16/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በ10ኛው ቀን ህዳር 27/03/2017 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ በዚያው ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ህዳር 30/2017 ዓ.ም በአርብ ገበያ ከተ /መ/ማ/ ቤት ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ካልተስማማበት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 28 54 63 51 መደወል ይችላሉ፡፡
አርብ ገበያ ከተማ መሪ/ማ/ቤት