የሊዝ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
145

የቡሬ ከተማ አስ/ከተ/መ/ል/ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መመሪያ ቁጥር 01/2005 መሰረት በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
የጨረታ ዓይነት መደበኛ
የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
በጨረታው ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ነው፡፡
ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ቡሬ ከተ/አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ግቢ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በቡሬ ከተ/አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡
መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ለድርጅት አምስት በመቶ ለመኖሪያ አምስት በመቶ በማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
የግንባታ ደረጃ ለድርጅት G+3 እና በላይ ለመኖሪያ G+0 ነው፡፡
የቦታው አገልግሎት በእያንዳንዱ ምድብ ከሰነዱ ጋር በሚሸጠው ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡ ለጨረታ የወጣው የቦታ ብዛት ለድርጅት 06 መኖሪያ 11 ነው፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 00 06 /058 774 03 48 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቡሬ ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here