የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የወገዳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በደነገገው የሊዝ አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 ደንብ ቁጥር 103/4004 እና ይህን አዋጅና ደንብ ለማስፈጸም የወጣ መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ለመኖሪያ 11 ለድርጅት 1 በድምሩ 12 ቦታዎችን በጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 1 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ11 ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታን በተመለከተ ወገዳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- ማስታወቂያው ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሀሳቦች /ህጎች/ ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጽ/ቤቱ የማስታወቅያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 667 00 39 /09 40 82 69 67 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወገዳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

