የሞጣ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ እስክ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያና ንግድ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሞጣ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በስራ ስዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ኘሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በከተማ አስተዳደሩ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚመለሰው የጨረታ አሸናፊው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ10 በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ሰነድ ከዋጋ እና ከሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ 058 661 20 40 /058 661 00 27 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሞጣ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

