የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ 72/2004 መሠረት በ2017 በጀት ዓመት ለሁለተኛ ዙር ከ1-5 የተዘረዘሩትን የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ ሸህ ሰኢድ አበበ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ፍቃዴ እንዲሁም በደቡብ ትሁኔ መካከል የሚገኝ ቦታ ስፋቱ 400 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ እነ እስከዳር ታደሰ ፣በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ዝቤ እንዲሁም በደቡብ ምስጋና መካከል የሚገኝ ስፋቱ 300 ካ/ሜትር፣
- ቀበሌ 01 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ ፣በምዕራብ ንጉስ አግማስ፣ በሰሜን አዱኛ አንዲሁም በደቡብ ክፍት ቦታ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 500 ካ/ሜትር፣
- ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ ቢላል መኮነን ፣በምዕራብ አሊድ ኑርልኝ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ቢያድግ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 224 ካ/ሜትር፣
- ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ ፣በምዕራብ ቀበሌ ቤት ፣በሰሜን ግዛቸው እንዲሁም በደቡብ የልፍኝ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 108 ካ/ሜትር፣
- የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 በመምጣት የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ አይነት መደበኛ፣
- የጨረታ ሰነድ የመግዣ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን 11፡30 ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ለሚወዳደሩበት አምስት በመቶ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ያስያዙት ሲፒኦ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- የግንባታ ደረጃ ለድርጅት እና ቅይጥ ቤት፡፡
- የቦታው አገልግሎት በእያንዳንዱ ምድብ ከሰነዱ ጋር በሚሸጠው ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
- ከላይ በአዋሳኝ የተጠቀሱትን ቦታዎች የሚያሸንፉ ተጫራቾች አርባ በመቶ ቅድሚያ ክፍያ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 446 00 26 ደውለው ማግኝት ይችላለሁ፡፡
የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት