የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ 5 ለድርጅት 1 የድርጅት ልዩ ጨረታ 1 በድምሩ 7 ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል በመሆኑም፡-
- መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል አ/ዘ/ከ/አስ/መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ማስታወቂያው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሸት 11፡00 ብቻ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ከጠዋቱ በ3፡00 ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 31 73 72 ወይም 09 27 60 08 17 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት