የክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በሊዝ መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 7 ለድርጅት 2 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 9 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽት 11፡30 በሥራ ሰዓት ከተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መሪ ማ/ቤት አዳራሽ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ቦታውን በመስክ ለመጎብኘት ከፈለጉ ከክምር ድንጋይ ማዘጋጃ ቤት ድረስ በመምጣት ከጨረታ ኮሚቴው ጋር መጎብኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅት 15 በመቶ ለመኖሪያ 10 በመቶ ህጋዊ በሆነ ባንክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ወይም በስ.ቁ 09 18 71 44 11 ደውለው ማግኘት ይችላሉ
የክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት