የጨረታ ዙር የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ
የጨረታዉ ዓይነት መደበኛ ጨረታ
- የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር /ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረዉ መሰረት ለመኖሪያ 12 ( አስራ ሁለት) እና ለድርጅት7 የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ እድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ከመስከረም 19/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 /የስራ ቀናት/ ውስጥ የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለመኖሪያ 300 /ሶስት መቶ/ ብር፣ ለድርጅት 500 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል በእንጅባራ /ከ/አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ከ/መ/ል/ባ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 004 ዘወትር በስራ ቀን እስከ 11፡00 መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታወቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቀኑ እስከ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ የሚዘጋዉ ሰነድ ሽያጭ ባለቀበት ቀን ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎችን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመ በኋላ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ከባለሙያ ጋር መጐብኘት ይቻላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ከታሸገበት በቀጣዩ ቀን ከጥዋቱ 3፡00 የመኖሪያ በቀጠዩ ቀን የድርጅት ደግሞ በእንጅባራ ከ/አስተዳደር አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታዉን ዝርዝር መረጃ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ማንኛውንም መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር፡ (251) 058 227 00 05 መደወል ይችላሉ፡፡
የእንጅባራ ከተማ አስተዳድር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት