የሊዝ  ጨረታ ማስታወቂያ

0
84
  1. የጨረታ ቁጥር፡ ደማ/01/2018
  2. የጨረታ ዙር፡ 1ኛ
  3. የጨረታ ዓይነት፡ መደበኛ
  4. የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ፣ ማህበራዊ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከአገልግሎት አቅርቦት ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በሥራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በ10ኛው ቀን  የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 10፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት በ10 ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ነው፡፡
  7. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በመምሪያው ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ዉጤት ከሀያ በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይሆናል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ  ልማት መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here