የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር ከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በ2016 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት 4 .እና ለመኖሪያ 2. ጠቅላላ 6 ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 250.00/ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በከተማው መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 444 02 63 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡