የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር ከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት 3 ፣ለመኖሪያ 5 ጠቅላላ 8 ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት10 የስራ ቀናት ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን በ3፡0 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤትግቢ ከጧቱ በ3፡00 ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 444 02 63 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
የአዲስ ዘመን ከ/አስ/ ከ/ መሰ/ል ጽ/ቤት

