የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ 72/2004 መሠረት በ2016 በጀት ዓመት ለሦስተኛ ዙር ከ 1-6 የተዘረዘሩትን የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ እነ በልሲቲ ጌትነት፣ በምዕራብ ይስማው፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ፖስታ ቤት፣ መካከል የሚገኝ ቦታ ስፋቱ 157.5 ካ/ሜትር ቦታ፡፡
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ ውዱ ትዛዙ፣ በምዕራብ ዓለምየ አሊ፣ በሰሜን የቀበሌ ቤት፣ በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 164.5 ካ/ሜትር ቦታ፡፡
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ዓብይ፣ በሰሜን አስማማው ዓለሙ፣ በደቡብ ጌትነት አሳፈው መካከል የሚገኝ ስፋቱ 115.1 ካ/ሜትር ቦታ፡፡
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ ወሰን የለሽ፣ በምዕራብ ቦሰናና አምባው፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ የቀበሌ ቤትና አህመድ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 560 ካ/ሜትር ቦታ፡፡
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ካሳነሽ ገረመው እና አሰፋ፣ በሰሜን ወኪል ሙሀመድ፣ በደቡብ ጀማ ኑርያ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 185 ካ/ሜትር ቦታ፡፡
- ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አበባው በርሄ እና ጥሩየ አሌ፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ተሾመ ዳኛው መካከል የሚገኝ ስፋቱ 450 ካ/ሜትር ቦታ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 17 በመምጣት የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ አይነት መደበኛ፡፡
- የጨረታ ሰነድ የመግዣ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን 11፡30 ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ለሚወዳደሩበት አምስት በመቶ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ያስያዙት ሲፒኦ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- የግንባታ ደረጃ ለድርጅት እና ለመኖርያ ቤት
- የቦታው አገልግሎት በእያንዳንዱ ምድብ ከሰነዱ ጋር በሚሸጠው ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 446 00 26 ደውለው ማግኝት ይችላሉ፡፡
የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት