የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ 72/2004 መሠረት በ2017 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ከ1 እስከ 9 የተዘረዘሩትን የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፤
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ ፈንታየ ፣በምዕራብ መንገድ ፣ በሰሜን የተመኝ ፣በደቡብ ጴጥሮስ መካከል የሚገኝ የድርጅት ቦታ ስፋቱ 252.5 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ ኑርሴንና አዝመራው ፣በምዕራብ ሀብቴ አስካለማርያም ፣በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ እንድሪስ ሰይሱ መካከል የድርጅት ቦታ ስፋቱ 120 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ ፣በምዕራብ ታረቀኝ አለሜ ፣በሰሜን እናኑ ፈረደ ፣በደቡብ አስማረ ይርደው መካከል የሚገኝ የድርጅት ቦታ ስፋቱ 64 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ እነበልስቲ ፣በምዕራብ ይስማው ፣በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ ፖስታ ቤት መካከል የሚገኝ የድርጅት ቦታ ስፋቱ 157.5 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ ውዴ ትዛዙ ፣በምዕራብ አለምየ አሊ ፣በሰሜን የቀበሌ ቤት ፣በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ የድርጅት ቦታ ስፋቱ 164.5 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ ወሰንየለሽ ፣በምዕራብ ቦሰናና አንባው ፣በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ እነ አህመዲና የቀበሌ ቤት መካከል የሚገኝ የድርጅት ቦታ ስፋቱ 560 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ ማስረሻ ፣በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን የግር መንገድ ፣በደቡብ ካሳ በለጠ መካከል የሚገኝ የድርጅት ቦታ ስፋቱ 90 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ ፣በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን ዝይን አሰፋ ፣በደቡብ እነ አመልማል መካከል የሚገኝ ቅይጥ ቦታ ስፋቱ 155 ካ/ሜትር
- ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ አዘነጋሽ ፣በምዕራብ አሰፋሽ ፍቅሬ ፣በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ እቴናት መካከል የሚገኝ የድርጅት ቦታ ስፋቱ 96 ካ/ሜትር ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባችኃል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 በመምጣት የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ አይነት መደበኛ፡፡
- የጨረታ ሰነድ የመግዣ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን 11፡30 ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ወ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ለሚወዳደሩበት አምስት በመቶ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ያስያዙት ሲፒኦ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- የግንባታ ደረጃ ለድርጅት እና ቅይጥ ቤት
- የቦታው አገልግሎት በእያነዳንዱ ምድብ ከሰነዱ ጋር በሚሸጠው ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
- የቦታው ስፋት ከ160 ካሬ ሜትር የሆኑ ቦታዎችን የሚያሸንፍ ተጫራች አርባ በመቶ ቅድሚያ ክፍያ መክፈል ይኖርበታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 446 00 26 ደውለው መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት