የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
98

የሰሜን ወሎ ዞን የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት የሊዝ ጨረታ ኮሜቴ የከተማ ቦታን በሊዝ ሰለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከሀ እስክ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም አካል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ ማወቅ እና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ 600.00 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል በመሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ተ.ቁ የጨረታው አይነት የጨረታው ዙር የቦታው መገኛና ቀበሌ የቦታው ስፋት የቦታው አገልግሎት ለቦታው የተሰጠው የጨረታ ኮድ ቁጥር
1 መደበኛ 2ኛ ዙር 02 ቀበሌ መነሀሪያ የነበረው 238275 ካ.ሜ ለሆቴልና ለተለያዩ አገ/ቶች 01
2 መደበኛ 2ኛ ዙር 01 ቀበሌ ከሚካኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ 934.37 ካ.ሜ ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አገ/ቶች 02

 

  1. ጨረታ ዙር፦ 2ኛ ዙር የ2017 ዓ.ም
  2. የጨረታው ዓይነት – መደበኛ
  3. ቦታው ከማንኛውም ክርክር ነፃ ነው
  4. የቦታው ደረጃ 1ኛ
  5. በቦታ የሚፈቀደው አገልገሎት አይነት የህንፃው ከፍተኛ የግንባታ ወለል ግቢ ስፋት ንጽጽር በፐርሰንት ሆኖ ቦታው ሆቴል፣ ለምግብ አዳራሽ ለመኝታ አገልገሎት የሚውል ሲሆን ከፍታውም G+4 ፎቅና ከዚያ በላይ ሆኖ 70 በመቶ የቦታው ስፋት በግንባታ ይሸፈናል፡፡
  6. የጨረታው መነሻ የሊዝ ዋጋ ለ1 ካሬ 500 አምስት መቶ ብር) ብቻ ነው፡፡
  7. የሚፈለገው አነስተኛ የቅድሚያ ክፍያ መጠን አጠቃላይ የቦታውን ዋጋ ሃያ በመቶ ይሆናል፡፡
  8. የቀረ ክፍያ ማጠናቀቂያ መጀመሪያ ክፍያ ከተከፈለበት ከ2 ዓመት የአፎይታ ጊዜ በኋላ ጀምሮ አስከ ሊዝ ዘመኑ 40 አመት (አርባ) ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ አንደተገለፀለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ዋጋ ከሃያ በመቶ ያላነስ ቅድሚያ ከፍያ ወይም በቴክኒካል ፕሮፖዛል ላይ የገለፀውን ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም ውል ይዋዋላል፡፡ በተጠቀሰው ቀን በሚስጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል ፣2ተኛ የወጣው አንደኛ የመጣውን ዋጋ በመስጠት መውሰድ ከፈለገ ይሰጠዋል፡፡
  10. ተጫራቹ የጨረታ ማስከበረያ ሲፒኦ የተጫረተበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማብዛት የሚገኘውን ውጤት አምስት በመቶ ያላነሰ በኦርጅናል ፖስታ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  11. ተጫራቹ የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽጎ በጽሁፍ ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡
  12. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደልና በአሀዝ መሙላት ይኖርበታል፡፡ በፊደልና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  13. አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይቻልም ገዝቶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  14. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጀምርበት ጊዜ 19/05/2017 ዓ.ም እስክ 30/05/2017 ዓ.ም በአስር የሥራ ቀናት ከቀኑ አስከ አስራ አንድ ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  15. በሰነድ ማሳሰቢያው ሀሳብ ላይ በፊደልና በአሀዝ የተፃፈው ሥርዝ ድልዝና የሚያምታታ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  16. የጨረታው የሰነድ ሽያጭ የሚያልቅበት ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
  17. ሰነዱን በመሬት ልማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) በመምጣት በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
  18. ቦታውን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በማንኛውም የሥራ ስዓት በአካል በመቅረብ የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  19. ጨረታው የሚከፈተው የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 በመርሳ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  20. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ከሆነ ስልክ ቁጥራችን 033 333 00 68 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  21. መሥሪያ ቤቱ በጨረታው ካልተስማማ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here