በአፈ/ከሳሽ አንድነት እቁብ ማህበር እና በአፈ/ ተከሳሾች 1ኛ. አሰፋ አድማስ ፣2ኛ. ዘውዴ መኮነን መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ ንብረትነቱ የ2ኛ. ተከሳሽ ዘውዴ መኮነን የሆነ መኖሪያ ቤት በአዋሳኝ በምስራቅ መንግስቱ ምትኩ ፣በሰሜን አዲሴ ሀይማኖት ፣ በደቡብ ስሜነህ የትዋለ እና በምዕራብ መንገድ ተዋስኖ የሚገኘው ቤት በመነሻ ዋጋ 756290.00 /ሰባት መቶ ሀምሳ ስድስት ሽህ ሁለት መቶ ዘጠና ብር/ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ ታህሳስ 30 ከጠዋቱ 3 ፡00 እስከ 6፡00 ስለሚሸጥ ፤ ማንኛውም ተጫራች በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ቤቱ ከሚገኝበት ቦታ በመገኘት እና የግምቱን ¼ኛውን በማስያዝ መጫረት እና መግዛት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
አዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት