የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
116

በአፈ/ከሣሽ የሀሎ ጀኔራል ሴኩሪቴ ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና በአፈ/ተከሣሾች 1. አሽርፍ አግሪካቸራል እና ኢንዱስትሪያል ኃ/የተ/የግ/ማህበር 2. ባ/ዳር ምግብ ዘይት አ/ማ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የ1ኛ አፈ/ተከሣሽ አሽርፍ አግሪካቸራል እና ኢንዱስትሪያል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ንብረቶች የሆኑትን 1ኛ HDP pipe ብዛቱ 200 በመነሻ ዋጋ ግምቱ ብር 800‚000/ስምንት መቶ ሺህ ብር/፤ 2ኛ ፎር ክሊፍት forklift CAT ብዛት 02 በመነሻ ዋጋ ብር 1‚080‚000/አንድ ሚሊየን ሰማንያ ሺህ ብር/ እንዲሁም 3ኛ ፎር ክሊፍት forklift NISSAN ብዛት 02 በመነሻ ዋጋ 900‚000/ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር/፤ ንብረቶቹ በሚገኙበት በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አዲስ ዓለም ቀበሌ አስተዳደር መነሻ ዋጋቸውን መነሻ በማድረግ ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ የፍ/ቤቱ ሃራጅ ባይም ጨረታው በሚካሄድበት በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አዲስ ዓለም ቀበሌ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት ጨረታውን በበላይነት በመምራት በእለቱ ለመጫረት የሚቀርቡትን ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዛቸውን በማረጋገጥ አጫርተው ውጤት ሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ/ም እንዲቀርቡ አዝዟል፡፡ በዕለቱ ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፈበትን ¼ኛውን በሞዴል 85 ጨረታው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ እንዲያስይዝ የደረጋል፡፡ ይንን ለማስፈጸም አንድ ፖሊስና ከክፍለ ከተማው /የቀበሌው/ ዋና አስተዳዳሪ ደግሞ አንድ አንድ ተወካይ በመላክ የጨረታውን ሂደት እንዲከታተሉ ፍ/ቤቱ በግልባጭ አዝዟል፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here