በከሣሽ ይንገስ ጌታሁን ህፃን ቴዎድሮስ አይንዋጋ እና በተከሣሽ ዝይን ደርሰህ ህፃን እየሩሣሌም አይንዋጋ ዳግማዊት አይንዋጋ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በእነ ዝይን ደርሰህ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ካርታ ቁጥር አፄ/ቴ 9800/2015 ክ/ከ/ቀበሌ አዲስ አለም በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አዛለች ጌታሁን፣ በሰሜን አዝመራ ዘለቀ እንዲሁም በደቡብ ትልቅሰው አፈረ የሚያዋስነው 56.60 ካሬ ሜትር ቦታ በግምት መነሻ ዋጋ ብር 545,258.71/አምስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ ስምንት ብር ከ71/100 ሣንቲም/ ሆኖ ህዳር 13/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በስዓቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የመጨረሻ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን በሞዴል 85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያሣውቃል፡፡
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት