የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
7

በአፈ/ከሣሽ ቢሻው ወርቄ እና በአፈ/ተከሣሽ አንሙት የኔነህ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 ፤ በምስራቅ ተፈሪ ጸጋ በምዕራብ ጥላየ ሞሴ ፣በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ነጻነት አንዷለም መካከል የሚገኝ እና በአቶ አንሙት የኔነህ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,155,472.62 / አንድ ሚሊዬን አንድ መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰባ ሁለት ብር ከስልሳ ሁለት ሣንቲም/ ስለሚሸጥ የጋዜጣ ማስታወቂያው  ከጥቅምት 17/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 17/2018 ዓ.ም ቆይቶ ህዳር 18/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ይሸጣል፡፡ መጫረት የምትፈልጉ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ውን አስይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባንጃ ወ/ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here