በአፈ/ከሣሽ ተስፋዩ አብዬ እና በአፈ/ተከሣሽ ምህረቴ ገበየሁ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በማስተዋል አድማስ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ፤ በምስራቅ አዳነ አወቀ፣ በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን አዳነ አወቀ፣ እንዲሁም በደቡብ ቄስ አያሌው የሚያዋስነው እና 200 ካ.ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,200,000/አንድ ሚሊዬን ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ህዳር 20/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ መጫረት የምትፈልጉ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ፡፡የመጨረሻው አሸናፊ ያሸነፈበትን ¼ ኛውን በሞዴል 85 ወዲያውኑ ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያሣውቃል፡፡
የባሕር ዳርና አካ/ከፍ/ፍ/ቤት

