በአፈ/ከሣሽ ይንገስ ጌታሁን እና በአፈ/ተከሣሽ እነ ዝይን ደርሰህ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ አፄ/ቴ/ አዲስ አለም ቀበሌ በእነ ዝይን ደርሰህ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ካርታ ቁጥር አፄ/ቴ 9800/2015 በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አዛለች ጌታሁን፣ በሰሜን አዝመራ ዘለቀ እንዲሁም በደቡብ ትልቅ ሰው የሚያዋስነው 56.60 ካሬ ሜትር ቦታ በዜሮ መነሻ ዋጋ ጥር 9/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የመጨረሻ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን በሞዴል 85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያሣውቃል፡፡
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት

