የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
137

በአፈ/ከሣሽ እነ ህፃን ሰብለ ደጀን /በቁጥር 3 ሰዎች/ ሞግዚት እመቤት ተፈራ እና በአፈ/ተከሣሽ ገድቱ አማረ  መካከል ስላለው የገንዘብ አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በወልደያ ከተማ ልዩ ቦታው አይሴማ የሚገኘው 180 ካ.ሜ ቤትና ቦታ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ በየነ ሊበን፣ በሰሜን ካሳ መኮነን እና በደቡብ ሙሉጌታ አባተ የሚያዋስነው ቦታ በመነሻ ዋጋ 433,836.38 /አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ስምንት በመቶ ሰላሳ ስድስት ከሰላሳ ስምንት ሳንቲም/ ሆኖ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡ በመሆኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ/ም አየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጨረታው መሣተፍ /መግዛት/ የሚፈልጉ መጫረት የምትችሉ ሲሆን  የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን 25 በመቶ ወይም ¼ ኛውን ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ያለበት መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here