የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
42

በአፈ/ከሳሽ ንጋት መከረ  እና በአፈ/ተከሳሽ ጌቴ ይጀቡ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በባሕር ዳር ከተማ፣ ግሽ አባይ ክ/ከተማ ግዮን ቀበሌ በአፈ/ተከሳሽ ጌቴ ይጀቡ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ፤በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ንብረት ተባባል፣ በሰሜን አዳሙ ከበደ እንዲሁም በደቡብ ስዩም አለማየሁ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው 400 ካ/ሜትር፣  G+6 ቤትና ቦታ  በመነሻ ዋጋ 73‚804‚832.07 (ሰባ ሶስት ሚሊየን ስምንት መቶ አራት ሽህ ስምንት መቶ ሰላሳ ሁለት ብር ዜሮ ሰባት ሳንቲም) ሆኖ የካቲት 18/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ  ንብረቱ በሚገኝበት በባ/ዳር ከተማ ግሸ አባይ ክ/ከተማ ግዩን ቀበሌ በመገኘት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የመጨረሻው አሸናፊ ያሸነፈበትን ¼ ኛውን በሞዴል 85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን እንዲያውቁት ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here