በአፈ/ከሳሽ ታከለ ማንዴ እና በአፈ/ተከሳሽ ሹመት አለኸኝ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በባሕር ዳር ከተማ፣ በዳግማዊ ም/ክ/ከተማ አዲስ አምባ ቀበሌ የሚገኘውንና በአፈ/ተከሳሽ ሹመት አለኸኝ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን 120ካ∙ሜ ቦታ ላይ ያረፈ የመኖሪያ ቤት ጥር 26/2018 ዓ∙ም ጨረታው እንዲወጣና እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ወስኗል፡፡ የጨረታው መነሻ ዋጋ 1‚013‚573∙24 (አንድ ሚሊዩን አስራ ሶስት ሽህ አምስት መቶ ሰባ ሶስት ብር ከሃያ አራት ሳንቲም) ሲሆን መጫረት የምትፈልጉ የጨረታ ማስታወቂያው ከየካቲት 3/2018 ዓ∙ም እስከ መጋቢት 2/2018 ዓ∙ም በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ ፤መጋቢት 5/2018 ዓ∙ም ከ3፡00 አስከ 6፡00 ጨረታው ስለሚካሄድ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ከ/ወ/ፍ/ቤት

