በአፈ/ከሣሽ አቶ ታደሰ ደስታው ወኪል አለማየሁ ታደሰ እና በአፈ/ተከሣሽ ወ/ሮ ሃይማኖት ታደሰ መካከል ስላለው የቤት ሽያጭ ገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በአፈ/ተከሣሽ ወ/ሮ ሃይማኖት ታደሰ ንብረት የሆነው ቶዮታ ሚኒባስ መኪና የሰሌዳ ቁጥር ኮዱ3-106090 አ.ማ የሆነች የሞዴል ቁጥር KR-KDH 200V-SRMDY የሆነ ፣ የቻንሲ ቁጥር KDH 200-0007863 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመነሻ ብር 1,700,000/አንድ ሚሊየን ሰባት መቶ ሸህ ብር/ሆኖ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
ስለዚህ የጨረታ ማስታወቂያው ለ15 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ድረስ ይከናወናል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሣተፍ/መግዛት/ የሚፈልግ ሁሉ ንብረቱ በሚገኝበት በደሴ ከተማ በደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ በመገኘት መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ኛው ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባይ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ያለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡