የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
138

በአፈ/ከሣሽ እነ መልካሙ ባየው /70 ሰዎች/  እና በአፈ/ተከሣሽ እነ ላቄው ፀጋየ /3 ሰዎች/ መካከል ስላለው የአፈፃፅም ክስ ክርክር ጉዳይ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፋሲሎ ክፍለ ከተማ በሰፈነ ሰላም ቀበሌ አሮጌው መናኸሪያ ፊት ለፊት በካርታ ቁጥር 33580/09 በሆነ 268 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈ G+6 ህንፃ ፍላሚንጎ ሆቴል ማስፋፊያውን ጨምሮ 930 ካ.ሜ ቦታ ጋር 70 በመቶ በ1ኛ አፈ/ተከሳሽ ላቄው ፀጋየ አየለ እና 30 በመቶ በ2ኛ አፈ/ተከሳሽ በአቶ ለገሰ ሞላ ባዜ ስም ተመዝግቦ የሚያዋስነው ቤት በመነሻ ዋጋ 51,233,290 /ሃምሳ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠኝ ብር/ ጨረታ መነሻ ዋጋው በሐራጅ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዝዟል:: በመሆኑም የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያው ለ30 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል:: ስለዚህ በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ንብረቱ በሚገኙበት በባሕር ዳር ከተማ ፋሲሎ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 በመገኘት ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኝት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን  የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን በሞ/85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል::

የባሕዳርና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here