በአፈ/ከሳሽ መሳፍንት ቢረሳው እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ መንግስቱ ካሳሁን መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ 008 ፣በምዕራብ 006 ፣በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚያዋስነውን በአቶ መንግስቱ ካሳሁን ሥም ተመዝግቦ የሚገኝ የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,450,000 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ስለሚሸጥ የጨረታ ማስታወቂያው ከሀምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ማስታወቂያ በማውጣት ጫታው ነሀሴ 21/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:00 ጨረታው የሚካሄድ መሆኑ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሣሠቢያ:- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ተኛው /በሲፒኦ/ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት