በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንክ ነገረ ፈጅ ሙሉጌታ አስራት እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ ቻላቸው አለነ፣ 2ኛ ምሳየ መላኩ፣ 3ኛ የቤቴ አሳየ ወራሽ አያል ፋሪስ፣ 4ኛ አለና ቢያድግልኝ፣ 5ኛ ቄስ መላኩ እባቡ እና 6ኛ አሳየ ቢያድግልኝ በአፈ/ተቃዋሚ ገነት ፈንታው መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የ6ኛ የአፈጻፀም ተከሳሽ አሳየ ቢያድግልን ሀብት ንብረት የሆነውን በሙጃ ከተማ ግዳን ወረዳ ቀበሌ 01 በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ የሙጃ እና የአካባቢዋ ማህበረሰብ ህብረት ሥራ ማህበር ጽ/ቤት፣ በሰሜን የዘውዲቱ ፈንቴ እና በደቡብ የበላይነሽ ፈንቴ በአዋሰነ መካካል በግምቱ 320,789.50 /ሦስት መቶ ሀያ ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ መነሻ ዋጋ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያው ከሀምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ነሀሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ወይም መግዛት የምትፈልጉ ቤቱ ወይም ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በሙጃ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ አሸናፊው የአሸነበትን 25 በመቶ ለሃራጅ ባዩ ወዲያውኑ የሚያስረክብ ሲሆን ቀሪውን ክፍያ ሕጉ በሚደነግገው እና የፍ/ቤቱ ችሎት በሚያዘው መሰረት ለፍርድ ባለሃብቱ አጠቃሎ የሚከፍል መሆኑን ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የሰ/ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት