በአፈ/ከሳሽ አቶ ካሳሁን አዳሙ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አብየ ቢተው 2ቱ መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ ጥሩየ ተገኘ ፣በምሥራቅ ዘለቀ አስማረ እና በምዕራብ ሙሉ ወንድም የሚያዋስነው በአቶ ቢተው ዋሲሁን አካል ሥም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 1‚267‚847 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ሰባት ሽህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት ብር/ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው ከሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ታትሞ ይቆይና ፤ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 5፡00 ጨረታው ስለሚካሄድ መግዛት የምትፈልጉ በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ፤ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን /በሲፒኦ/ አስይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት