በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንክ ነገረ ፈጅ ሙሉጌታ አስራት እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ ቻላቸው አለነ፣ 2ኛ ምሳየ መላኩ፣ 3ኛ የቤቴ አሳየ ወራሽ አያል ፋሪስ፣ 4ኛ አለና ቢያድግልኝ፣ 5ኛ ቄስ መላኩ እባቡ እና 6ኛ አሳየ ቢያድግልኝ በአፈ/ተቃዋሚ ገነት ፈንታው መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የ5ኛ ተከሳሽ የቄስ መላኩ እባቡ ሀብት ንብረት የሆነውን በሙጃ ከተማ ግዳን ወረዳ ቀበሌ 01 በምሥራቅ ቄስ መላኩ እባቡ፣ በምዕራብ አብራሬ፣ በሰሜን መንገድ እና በደቡብ የእግር መንገድ አዋሳኝ በግምቱ 662,842.91 /ስድስት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሁለት ብር ከዘጠና አንድ ሳንቲም/ መነሻ ዋጋ ሆኖ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያው ከሀምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ወይም መግዛት የምትፈልጉ ቤቱ ወይም ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በሙጃ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ አሸናፊው የአሸነበትን 25 በመቶ ለሃራጅ ባዩ ወዲያውኑ የሚያስረክብ ሲሆን ቀሪውን ክፍያ ሕጉ በሚደነግገው እና የፍ/ቤቱ ችሎት በሚያዘው መሰረት ለፍርድ ባለሃብቱ አጠቃሎ የሚከፍል መሆኑን ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የሰ/ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት