በአፈ/ከሳሽ አንድነት እቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ 1ኛ. አሰፋ አድማስ ፣2ኛ. ዘውዴ መኮነን መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 04 በሰሜን አዲሴ ሀይማኖት ፣በምሥራቅ መንግስቱ ምትኩ ፣በደቡብ ስሜነህ የትዋለ እና በምዕራብ መንገድ የሚያዋስነው የ2ኛ. አፈ/ተከሳሽ ዘውዴ መኮነን ንብረት የሆነ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 986,220 (ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ስድስት ሽህ ሁለት መቶ ሀያ ሽህ ብር) በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው ከነሀሴ 15/2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 10/2018 ዓ.ም በጋዜጣ ታትሞ ይቆይና መስከረም 11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ስለሚሸጥ መግዛት የምትፈልጉ የግምቱን ¼ኛውን በማስያዝ በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት