የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
95

አውራ አምባ ማ/ፋ/ኢ /አ/ማ እነ አቶ ግዛቸው አጥናፍ የተበደሩትን ገንዘብ ባለመክፈላቸው ለብድሩ መያዣ የሆነውን  ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሠረት ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ በሐራጅ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች የቤቱን ይዞታ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መመልከት ይችላሉ፡፡

የተበዳሪው ስም የንብረቱ ባለቤት የካርታ ቁጥር የቦታ ስፋት አድራሻ ቀበሌ የጨረታው መነሻ ዋጋ የጨረታ ቀንና ሰዓት
ቀን ሰዓት
  እነ ግዛቸው አጥናፍ ወ/ሮ ዙፋን ብርሃኔ አፄቴ/11279/16 250 ካ.ሜ

መኖሪያ ቤት

ባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክ/ከ ልዩ ቦታ ማራኪ 4,876,346 ጥቅምት 21/2018 ከ3-5

 

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ዕለት የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ የቤቱን ግምት 20 በመቶ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ በማስያዝ በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 14 ኖክ አካባቢ ሪየስ ኢንጅነሪንግ አጠገብ እናት ባንክ ከሚገኝበት ህንጻ 1ኛ ፎቅ የማይክሮ ፍይናንስ ዋና መ/ቤት በመምጣት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት፡፡
  3. በሓራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተበዳሪ፣ንብረት አሰያዥ ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸውና የተመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው፡፡ ተበዳሪና ተወካዮቻቸው ባይገኙም በሌሉበት ጨረታው ይካሄዳል፡፡
  4. ለጨረታው አሸናፊ በማይክሮ ፋይናንሱ የብድር ፖሊሲ መመሪያና ቅድመ ሁኔታ መሰረት ብድር ሊመቻችለት ይችላል፡፡
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በጨረታው የመጨረሻ 30 ደቂቃ ውሰጥ የተጫራቾች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
  6. የሓራጅ አሸናፊ ወይም ገዥ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የግብር ግዴታዎችን ገዥው ይከፍላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ5 (አምስት) ቀን በፊት ከማ/ፋ ጋር በመነጋገር በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለጨረታ የቀረበውን ንብረት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የሚታወቀው አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ነው፡፡
  9. አጫራቹ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ጨረታው የሚከናወነው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ቢሮ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ 0916823282 እና 0918790003 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አውራ አምባ ማ/ፋ አ/ማ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here