በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንክ ደብረሮሀ ቅርጫፍ ነ/ፈጅ ሶፎኒያስ ጎሹ እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ. ገብረ ማርያም ሰጠኝ ፣ 2ኛ. ደጀን አበበ መንገሻ፣ 3ኛ. ጣሰው ማረጉ ጌታው 4ኛ. እንጉዳ ይልማ ደሳለ፣ 5ኛ. ትርንጉ ደሳለ አለሙ፣ 6ኛ.ጉዳይ ሲሳ እማኙ፣ 7ኛ. በቀለ ቸሩ አለሙ፣ 8ኛ. አበበ ገላው ደመነ፣ 9ኛ.ጥላሁን ወሰኔ ብርሃኑ እንዲሁም 10ኛ. በላይነሽ መላክ አረቂ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በሰሜን ወሎ ዞን ላልይበላ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ቦታው ደብረ ሲና እየተባለ ከሚጠራው ቦታ በምሥራቅ የተከዜ መነኮሳት ቦታ፣ በምዕራብ የእግር መንገድ፣ በሰሜን ሰማይነሽ ሰማው እና በደቡብ አባ ሀፍተ ጊወርጊስ የሚያዋስነውን በወ/ሮ ጎዳዳ ሲሳይ ስም በካርታ ቁጥር ላከ/አ/በአ/1662/2002 በ25/06/2002 ዓ.ም ተመዝግቦ የሚረኘውን የጭቃ ኤል ሸኘ ቤት በብር 840,892.5 (ስምንት መቶ አርባ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከአምስት ሳንቲም) መነሻ ዋጋ በጨረታ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፤ ስለዚህ የጨረታው ማስታወቂያ ከጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 30 ቀን በጋዜጣ ታትሞ ይቆይና፤ ጨረታው ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ ይካሄዳል፤ ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት የሚካሄድ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ አሸናፊ የአሸነፈበትን 25 በመቶ ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ያለበት መሆኑን እናሳውቃለን
የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት