የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
6

በአፈ/ከሣሽ አቶ አበበ ተላከ እና በአፈ/ተከሣሽ አቶ ሙሉቀን አንዳለው በዛ መካከል ስላለው  የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በአፈ/ተከሣሽ ሙሉቀን አንዳለው ስም በዳንግላ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 በአዋሣኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ከአቶ አታላይ አንዱዓለም፣ በደቡብ አቶ ፈንታሁን ተስፋዩ እንዲሁም በሰሜን ገረመው የሚያዋስነው ቤት በመነሻው ግምት 8,158,984.98 /ስምንት ሚለዮን አንድ መቶ ሃምሣ ስምንት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት ብር ከዘጠና ስምንት ሣንቲም/ ይሸጣል፡፡ ጨረታው ከጥቅምት 17/2018 ዓ.ም አስከ ህዳር 16/2018 ዓ.ም በጋዜጣ ወጥቶ የጨረታ ማስታወቂያውን በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ፣ በወረዳ ፍ/ቤት ቅጥር ግቢ፣ በመሃል ከተማ፣ በመኖሪያ ቤቱ፣ አንዲሁም ሕዝብ በሚበዛበት ቦታ ሁሉ በመለጠፍ ጨረታው በህዳር 17/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 የጨረታ ቦታው በመኖሪያ ቤቱ ላይ በማድረግ የጨረታ አሸናፊ 1/4 ኛውን ወዲያውኑ አንዲያስይዝ አና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ አንዲቀርብ በማድረግ በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው በመገኘት መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here