በአፈ/ከሳሽ መነሃሪያ ዙሪያ ይኸነው አናጋው ሆቴል የሚጣል እቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አጉማስ ሙሉነህ 3ቱ ራሳቸው መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ፤ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 ፤ በምሥራቅና በሰሜን መንገድ ፣በምዕራብ ክፍት ቦታ ፣ እንዲሁም በደቡብ የኔነሽ ኪነጥበብ መካከል የሚያዋስነው የድርጅት ቤት በአቶ ማርልኝ በዛ የተመዘገበ ቤት በመነሻ ዋጋ 1,848,734 /አንድ ሚሊዩን ስምንት መቶ አርባ ስምንት ሽህ ሰባት መቶ ሰላሳ አራት ብር/ ስለሚሸጥ፤ ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከጥቅምት 25/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 25/2018 ዓ/ም ቆይቶ ጨረታው ህዳር 26/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡00 የሚካሄድ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወ/ፍ/ቤት

