በአፈ/ከሳሽ አቶ አስቻለዉ ይስማዉ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ የኔጌት ተረፈ መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በከሳ ከተማ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ክፍት ቦታ እንዲሁም በደቡብ ሞላ አደን መካከል የሚገኝ በአቶ የኔጌት ተረፈ እና በቄስ ቢተዉ ሀይሌ በጋራ የተመዝገበ ወፍጮ ቤት የአፈ/ተከሳሽ ድርሻ ብቻ ግምቱ 1,051,971.85 /አንድ ሚሊዮን ሀምሳ አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ ብር ከሰማንያ አምስት ሳንቲም/ ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ መነሻ ዋጋዉን ሳይጠብቅ በጋዜጣ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ህዳር 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም ማስታወቂያ በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6፡30 የሚካሄድ መሆኑ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታ ስትሠጡ የጨረታሙን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

