በአፈ/ከሳሽ ጥላሁን ቢተው እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ደረጃ የኔት መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ አበራ ተገኘ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ደረጃ የኔት እንዲሁ በደቡብ ሙሉዓለም ቢተው መካከል ተዋስኖ የሚገኘው ቤት በመነሻ ዋጋ 2,900,000 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር/ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያ ከህዳር 08/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ በጨረታው መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ¼ ኛውን ብር በባንክ ሲፒኦ አስይዞ የመቅርብ ግዴታ ያለበት መሆኑን አውቆ በታህሳስ 09/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6:00 ድረስ ቀርቦ መቻረት እንደሚችሉ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

