በአብክመ ሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኘው የጃ/ወ/ት/ት ጽ/ቤት አገልግሎት የማይሰጡ ጊዜ ያለፈባቸው የተለያዩ መጽሐፎችን በሐራጅ ጨረታ አውዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በሙሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. በጨረታው ማንኛውም ግለሰብ መሳተፍ ይችላል እንዲሁም መጽሐፍ ያለበት ጃናሞራ ወረዳ መካነ ብርሃን ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሲሆን ጨረታው አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ መጋዘኑ ክፍት ይሆናል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ሰባት በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 ማስያዝ ይኖርባችዋል፡፡
3. አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ መጽሐፎች ሐራጅ ጨረታ ለአንድ ኪ.ግ መነሻ ዋጋ 3.00 /ሦስት ብር/ ሲሆን ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው ከ04/02/2017 ዓ.ም እስከ 18/02/2017 ዓ.ም ድረስ በአየር ላይ ይውላል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከ 04/02/2017 ዓ.ም እስከ 18/02/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 19/02/2017 ዓ/ም 4፡30 ታሽጎ 4፡45 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
8. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም ካለም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
10.መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11.አሸናፊ የሆነው ተጫራች ጊዜ ያለፈበችውን የተለያዩ መጽሐፎች ርክክብ የሚፈፀመው ያሽነፈበትን ጠቅላላ ብር ከገንዘብ ጽ/ቤት አካውንት ገቢ ሲያደረግ ጃናሞራ ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት መካነ ብርሃን ከተማ የሚረከቡ ሲሆን ማንኛውም ወጭ በተጫራች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
12.ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 058 294 00 23 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የጃን አሞራ ገንዘብ ጽ/ቤት