የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
56

በአፈ/ከሣሽ ሞላ ከበደ እና በአፈ/ተከሣሾች 1ኛ. አቶ አሰፋ አድማስ፣ 2ኛ. ደሳለው ዋሴ፣ 3ኛ. አለከኝ አይናለም በዛ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በዳንግላ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሣኝ በሰሜን ሽመልስ ደሴ፣ በደቡብ ማህበረ ቅዱሳን፣ በምሥራቅ አውራ ጐዳና እንዲሁም በምዕራብ መንገድ መካከል ያለው 360 ካሬ ሜትር ቤትና ቦታ የ1ኛ አፈ/ ተከሣሽ ቤት ብር 9,582,958.8 /ዘጠኝ ሚለዮን አምስት መቶ ሰማኒያ ሁለት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ስምንት ብር ከስምንት ሣንቲም/ መነሻ ዋጋ ይሸጣል፡፡  ጨረታውን ከህዳር 29/2018 ዓ.ም አስከ ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም በጋዜጣ አውጥቶ በማዋል ጨረታውን በጥር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 አስከ 6፡30 የጨረታ ቦታው በመኖሪያ ቤቱ ላይ በማድረግ ጨረታ አሸናፊ ከተገኘም ¼ ኛውን ወዲያውኑ አንዲያስይዝ አና በከፍተኛው ፍርድ ቤት በአማራ ባንክ አካውንት 9900017292828 በሆነ ገቢ እንዲያደርግና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ እንዲቀርብ በማድረግ በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ ሁሉ በቦታው ተገኝቶ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here