የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
90

ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ ለአቶ ወለላው በላይ እና ወ/ሮ ትዕግስት አበራ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛውን በሰንጠረዥ ከዚህ በታች የተገለፀ መኖሪያ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 

የተበዳሪው ስም የመያዣ ሰጪ ስም የካርታ ቁ/የይዞታው መለያ ቁጥር ቤቱ የሚገኝ በት ቦታ የቦታው ስፋት የንብረቱ አይነትና አገልግሎት የጨረታ መነሻ ዋጋ የጨረታ ቀንና ሰአት ጨረታ የወጣው
ወለላው በላይና ትዕግስት አበራ ወለላው በላይና ትዕግስት አበራ

 

AM010010504019 እንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ 200.875ከ/ሜ መኖሪያ ቤት 3,417,192.49 07/05/2018ዓም ከ4፡00-6፡00 ለሁለተኛ  ጊዜ

 

  1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) በፀደይ ባንክ አ/ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንናቱን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ አለባቸው፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቃለ ጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ አለበት፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት (ሲፒኦ) ይመለስላቸዋል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላሉ፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
  6. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት ጨረታው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ፣ ቀበሌ 01 በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ.ማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  8. ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበውን ንብረት የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊ በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ከሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
  9. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ዳቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
  10. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸነፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብደቤ በፁሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
  11. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብደቤ ይፅፋል፡፡
  12. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 227 07 08 ወይም 09 10 30 20 03 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here