በአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ ሀይማኖት ቅሩበር እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ብርሃኑ ማሬ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ፤በፍኖተ ሰላም ከተማ ቀበሌ 02 አዋሳኝ በሰሜን መንገድ ፣ በደቡብ አየሁ እጅጉ፣በምስራቅ ጀሚላ ሙሀመድ እና በምእራብ መልካም ዋሴ ተዋስኖ የሚገኘው 186 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተሰራው እና የአፈ/ተከሳሽ ንብረት የሆነው አንድ ትልቅ ቤትና 4 ክፍል ዶርም ፤በጨረታ መነሻ ዋጋ 999,791.00 /ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሽህ ሰባት መቶ ዘጠና አንድ ብር/ ይሸጣል፡፡የጨረታ ማስታወቂያው ከታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ቀናት ማስታወቂያው በጋዜጣ በአየር ላይ ቆይቶ፤ ጨረታው ጥር 15/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 እስከ 6፡00 ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ቤቱ በሚሸጥበት ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆንን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት