በአፈ/ከሣሽ በላይነሽ መኮነን እና በአፈ/ተከሣሾች እነ አንሙት የኔነህ 3ቱ ሰዎች መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በ1ኛ ተከሣሽ አቶ አንሙት የኔነህ ስም በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 በአዋሳኝ፡- በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ የእ/ይ ተሰራች አበጀሁ፣ በሰሜን የጌታቸው ኢትቻ እንዲሁም በደቡብ የአቶ ዘገይ ጥሩነህ የሚያዋስነው የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ 5,770,492.70 (አምስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሰባ ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከ70/100 ሳንቲም ) ሆኖ ጥር 8/2018 ዓ/ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ ማንኛውም ተጫራች ቦታው በሚገኝበት በመገኘት መጫረት የሚችል መሆኑን ፍ/ቤቱ አሣውቋል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት

