የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
50

አፈ/ከሳሽ አቶ አዝመራው ዳኛው እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ እነ ይቻላል ምናየሁ 2ኛ ወ/ሮ በላይነሽ ብዙየ 2ቱ ራሳቸው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መሰረት ቸኮል፣ በምዕራብ ገረመው ታመነ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ሀብታሙ መኮነን መካከል በአፈ/ተከሳሽ በወ/ሮ በላይነሽ ብዙየ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 2,258,769.40 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሀምሳ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከአርባ ሳንቲም) የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከታህሳስ 13/2018 እስከ ጥር 13/2018 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ 30 ቀናት ቆይቶ ጥር 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6፡00 እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ተኛው ይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዟል ፡፡

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here