የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
27

በአፈ/ከሣሽ አቶ አስፋው ታሪክ እና በአፈ/ተከሣሽ አቶ ጌትነት ዳኛው መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በአንክሻ ጓጉሳ ወረዳ ቀበሌ 02 የተከሣሽ ጌትነት ዳኛው የቤት ንብረት የሆነው በአዋሣኝ በምሥራቅ የአክሻ ጓጉሳ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት፣ በምዕራብ ውዱ ባብል፣ በሰሜን ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ 2,569,020.5 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ሃያ ብር ከሃምሳ ሳንቲም) በማድረግ ጨረታው ከታህሳስ 20/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 19/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ቆይቶ ጨረታው በጥር 20/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 አስከ 6፡00 በማጫረት የጨረታ አሸናፊ ከተገኘም ¼ ኛውን ወዲያውኑ እንዲያስይዙ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዘው እንዲቀርብ በማድረግ እና የይዞታ ማረጋገጫው አሁን ካለው የከተማ ማስተር ፕላን ጋር የማይጣጣም ወይም ይዞታውን መንገድ የሚቀንሰው እና ግንባታውንም መንገድ የሚመታው መሆኑን አውቀው ቦታው በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው ተገኝቶ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here