የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
75

በአመልካች/አፈ/ከሳሽ አማረ ሰንደቅ እና በተጠሪ አፈ/ተከሳሽ ፅጌረዳ አስረስ መካከል ስላለው የባ/ሚስት አፈጻጸም ክርክር ጉዳይ፤ በባሕር ዳር ከተማ  ቀበሌ አዲስ አለም፤ በአማረ ሰንደቅ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ፤በሰሜን ብርቱካን ምትኬ፣ በደቡብ ንጋቱ ወዝአፈራች፣ በምስራቅ መንገድ እና በምእራብ በላይ እንዳለው መካከል የሚገኝ G+1 የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 4‚658∙190 (አራት ሚሊየን ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ብር) በጨረታ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ የጨረታ መነሻ ዋጋውን በመያዝ ከጨረታው ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ ሲሆን፤ የጨረታው ቀንም ከታህሳስ 20/2018 ዓ∙ም እስከ ጥር 20/2018 ዓ∙ም በጋዜጣ ታትሞ ይቆይና፡፡ ጥር 20/2018 ዓ∙ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ጨረታው ይካሄዳል፤ መጫረት የምትፈልጉ  ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት ባሕር ዳር ከተማ አዲስ አለም ቀበሌ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ ወ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here