አፈ/ከሳሽ ሀይማኖት ክንዴ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አዲሱ ጋሹ 3ቱ ራሳቸው መካከል ባለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በምሥራቅ ሙሉ ወርቄ፣ በምዕረብ መንገድ፣ በሰሜን ገብሬ እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚዋስነው በአፈ/ተከሳሽ በአቶ አዲስ ጋሹ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የድርጅት ቤት የሆነው መነሻ ዋጋ ብር 2,248,380.97 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ ብር ከዘጠና ሰባት ሳንቲም) ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 27/2018 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ ጨረታው ጥር 28/2018 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 በመገኘት መጫረት የምትችሉ ሲሆን ውጤቱምን ለጥር 28/2018 ዓ.ም 8፡00 ላይ እንዲገለጽ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታ ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን (በሲፒኦ) አስይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

