በአፈ/ከሳሽ በረንዳ ዙሪያ አካባቢ ገበያ ማዕከል የሚጣል እቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አዲሱ አልጋነህ 2ቱ ራሳቸው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ የወንደሰን ግንብነህ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን የኋላ ካሳሁን፣ በደቡብ አቸነፍ ካሳሁን መካከል የሚያዋስነውን በአዲሱ አልጋነህ ስም የተመዘገበ ቤት በመነሻ ዋጋ 1,911,498 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አስራ አንድ ሺህ አራት መቶ ዘጠና ስምንት ብር) ይሸጣል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛዉም ተጫራች ጥር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 25/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ የካቲት 26/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ጫረታው የሚካሄድ መሆኑን አዉቃችሁ ቦታዉ ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች ወደ ጨረታዉ ስትመጡ የጨረታዉን መነሻ ዋጋ ¼ በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

