በአፈ/ከሣሽ በውቀት በላይ በአፈ/ተከሣሽ አላምነህ ይስማው በጣ/ገብ ብርሃኔ አሠጉ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈጻጸም ተከሣሽ ንብረት የሆነውን በአገው ግምጃ ቤት ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኘውን በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ባንቲገኝ ቢተው፣ በደቡብ መንገድ እና በሰሜን ባንቲገኝ ቢተው የሚያዋስነውን ቤት መነሻ ዋጋውን ብር 626,615.4 /ስድስት መቶ ሃያ ስድስት ሽህ ስድስት መቶ አስራ አምስት ብር ከአራት ሣንቲም/ በማድረግ መጋቢት 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 በሃራጅ ባይ ሰብሳቢነት የግምጃ ቤት ከተማ 02 ቀበሌ አስተዳደር ተወካይ፣ ከወረዳ ፍ/ቤት ሀራጅ ባይ ባለሙያ ተወካይ፣ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አንዳንድ ተወካይ በተገኙብት በጨረታ ስለሚሸጥ መግባት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው በመገኘት መግዛት የሚችል መሆኑን ፍርድ ቤቱ ያስታውቃል፡፡
የአዊ ብሔ አስ ከፍ/ፍ/ቤት