በአፈ/ከሳሽ አቶ አዱኛው አብጠው እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ አቶ ብርቁ ቢረስ እንዲሁም 2ኛ ወ/ሮ ደብሬ አስማረ መካከል ባለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 በአዋሳኝ በምሥራቅ ገድበው ድረስ፣ በምዕራብ ማህሬ አግዴ፣ በሰሜን መ/ታ ማህሬ አናጋው እና በደቡብ መንገድ መካከል በ200 ካ.ሜ ቦታ ላይ የተሠራ እና በአፈ/ተከሳሽ በአቶ ብርቁ ቢረስ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 836,586.00 /ስምንት መቶ ስላሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ብር/ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከየካቲት 03 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 02 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ በማውጣት መጋቢት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከ3፡00-6፡00 ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንድታሳውቁ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን /በሲፒኦ/ አስይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት